ኮቪድ-19 (አዲስ ኮሮናቫይረስ) - መረጃ፤ አገልግሎት፤ አና ንብረት የዋሽንግተን ስቴት

ከቤት መውጣት እና COVID-19 ክትባት መፈለግ አይቻልም? 

ለመመዝገብ ሶስት መንገዶች አሉ

የ COVID-19 የስልክ መስመር፦ ለሠራተኞች ፣ ለንግድ ሥራዎች ፣ ለክትባት ቀጠሮዎች እንዲሁም ለሌሎችም የሚሰጥ እገዛ 

ስል COVID-19 ጥያቄዎች ካልዎት ወይም የክትባት ቀጠሮን ለማስያዝ እገዛ ከፈለጉ, እባክዎን ለ 1-800-525-0127 በመደወል የ# ምልክቱን ይጫኑ። እነሱ መልስ ሲሰጡ, የአስተርጓሚ አገልግሎቶችን ለማግኘት የቋንቋዎን ስም ይጥሩ። የስልክ መስመሩ በየቀኑ ክፍት ነው እንዲሁም ሰዓቶቹ በ Department of Health ዌብሳይት ላይ (በእንግሊዝኛ ብቻ) ተዘርዝረዋል። 

የንግድ ሥራ ጥሰቶችን ሪፖርት ያድርጉ

የንግድ ድርጂቶች ለሠራተኞች እና ለደንበኞች ተገቢ የሆነ የጤና እና የደህንነት እርምጃዎችን መተግብር ይጠበቅባቸዋል። ጥሰቶችን ሪፖርት ማድረግ ከፈልጉ, በራስዎ ቋንቋ እገዛ ለማግኘት፣ እባክዎን ከላይ በተጠቀሰው የ COVID-19 የጥሪ መስመር ይደውሉ። የሆነ ሰው ሰለ ጥሰቱ ጥያቄዎችን ጠይቆ እርስዎን በመወከል ቅሬታዎችን ሊጠይቅዎት ይችላል። ቅሬታዎን ለማስገባት ፣ ስምዎን ወይም የእውቂያ አድራሻዎን ማጋራት አይጠበቅብዎትም።

እንዲሁም ቅሬታዎን በ እንግሊዘኛ ቋንቋ በ የ COVID-19 ጥሰቶችን ሪፖርት ያድርጉ ገጽ ላይ ማስገባት ይችላሉ

የእርስዎን ስም ወይም የእውቂያ መረጃ ካቀረቡ ፣ አንድ ሰው ለዚህ መረጃ ይፋዊ የመዝገብ ጥያቄ ካቀረበ መረጃው ለዛ ሰው በይፋ ሊገለጽ እንደሚችል እባክዎን ልብ ይበሉ። በ የገዢው የግላዊነት ማስታወቂያ ውስጥ በ (እንግሊዘኛ ብቻ) የተገለጹት ማስታወቂያዎች በመንግስት የሕዝብ መዝገቦች ፣ RCW 42.56 ስር በተዋቀረው ሕግ በተፈለገበት ጊዜ ይለቀቃል

ለሥራተኞች፣ ለንግድ ሥራዎች እና ለድርጂቶች የሚሰጡ ተጨማሪ እገዛዎች

የትርጉም ሥራ አገልግሎቶችን በመጠቀም ፣ የጥሪ መስመሩ ወደ አጠቃላይ መመሪያዎች እና ሃብቶች ሊመራዎት ይችላል። አሁንም ድረስ ጥያቄ ካልዎት የ COVID-19 የንግድ ሥራ እና የሰራተኞች ጥያቄዎችን ቅጽ በመሙላት ሊያግዝዎት ይችላሉ። መልስዎችን ለማግኘት እንዲረዳዎ የእውቂያ መረጃዎን ይጠየቃሉ።

የኮሮናቫይረስ (COVID-19) ክትባት

ስለ  COVID-19 ክትባቶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባክዎ የ COVID-19 የክትባት ገፃችንን.

WA Notify የስማርት ስልክ መተግበሪያ ማስታወቂያዎችን ያሳያል
Image
WANotify FlowChart AMHARIC FINAL

WA Notify (WA ማስታወቂያ) (Washington Exposure Notifications (የዋሽንግተን ተጋላጭነት ማሳወቂያዎች) ተብሎም ይጠራል) ለ COVID-19 የተጋለጡ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችን ለማስጠንቀቅ ማንኛውንም የግል መረጃ ሳይጋራ በስማርት ስልኮች የሚሰራ አዲስ መሳሪያ ነው፡፡  ሙሉ በሙሉ የግል ነው፣ እና እርስዎ ማን እንደሆኑ ወይም የት እንደሚሄዱ አያውቅም ወይም አይከታተልም።

WA Notify ን በስልኬ ላይ እንዴት ማከል እችላለሁ?

በ iPhone ላይ፣ በቅንብሮች/በሴቲንግስ ውስጥ Exposure Notifications ን ያንቁ/ያብሩ፦

 • ወደ Settings (ቅንብሮች) ይሂዱ
 • ወደ Exposure Notifications ወደታች ዝቅ ያድርጉ
 • “Turn on Exposure Notificationsን” ጠቅ ያድርጉ
 • ዩናይትድ ስቴትስን ይምረጡ
 • ዋሺንግተንን ይምረጡ

በ Android ስልክ ላይ፦

በ Android ወይም iPhone፣ QR ኮዱን ስካን ያድርጉ፡ -

WA Notify QR code

የሚሰራው እንዴት ነው?

የእርስዎን WA Notify፣ ሲያበሩ ስልክዎ በአቅራቢያዎ ካሉ የራሳቸውን WA Notify ካበሩ ሰዎች ስልኮች ጋር እንዲሁ የዘፈቀደ፣ የማይታወቁ ኮዶች ይለዋወጣል። መተግበሪያው ስለ እርስዎ ምንም መረጃ ሳይገልጽ እነዚህን የዘፈቀደ ኮዶች ለመለዋወጥ የ (BLE፣ ብሉቱዝ ሎው ኢነርጂ) ቴክኖሎጂን ይጠቀማል። ካለፉት ሁለት ሳምንቶች በኋላ እርስዎ አቅራቢያ የነበሩ ሌላ የ WA Notify ተጠቃሚ ለ COVID-19 አዎንታዊ ምርመራ ካደረጉ እና የመተግበሪያውን የማረጋገጫ ኮዱን በመተግበሪያው ላይ ካከሉ፣ ተጋላጭነቶች ሊኖርዎት እንደሚችል የማይታወቅ ማሳወቂያ ያገኛሉ፡፡ ይህ በፍጥነት የሚያስፈልግዎትን እንክብካቤ እንዲያገኙ ያስችልዎታል እንዲሁም COVID-19 ን በአካባቢዎ ላሉት ሰዎች እንዳያዛምቱ ያግዝዎታል።

ማስጠንቀቂያ ከማያስፈልጋቸው ደህንነቱ በተጠበቀ ርቀት ወይም አጭር ከሆነ COVID-19 ሊያስተላልፉ የሚችሉ ክስተቶችን ለመለየት አንድ ስልተ ቀመር ሂሳብን ይሠራል። WA Notify ተጋልጠው ከሆነ ብቻ ያሳውቀዎታል። ስለዚህ ማንቂያ አለመቀበል ጥሩ ዜና ነው።

WA Notify በተቻለ መጠን ብዙ የዋሽንግተን ነዋሪዎች ይህንን መሣሪያ ማግኘት እንዲችሉ በ 30 ቋንቋዎች በላይ ይገኛል።

ለአዎንታዊ የቤት ውስጥ የ COVID-19 ምርመራ ውጤት የማረጋገጫ ኮድ እንዴት እንደሚጠየቅ

የ WA Notify (የዋሺንግተን የተጋላጭነት ማሳወቂያ) ተጠቃሚዎች የሆኑ ያለ ማዘዣ የ COVID-19 መመርመሪያ ኪት የሚገዙ እና አዎንታዊ ውጤት የተቀበሉ በ WA Notify ውስጥ የማረጋገጫ ኮድ መጠየቅ ይችላሉ።

የማረጋገጫ ኮድ በመሳሪያ ለመጠየቅ፦

አንድሮይድ፦

 • WA Notify ን ይክፈቱ እና "Share your test result to help stop the spread of COVID-19 (የCOVID-19 ስርጭትን ለማስቆም የምርመራ ውጤትዎን ያጋሩ)" የሚለውን ይምረጡ።
 • “Continue (ቀጥል)” የሚለውን ከዚያ “I need a code (ኮድ እፈልጋለሁ)” የሚለውን ይምረጡ።
 • WA Notify የሚጠቀመውን መሳሪያዎን ስልክ ቁጥር እና አወንታዊ የ COVID-19 ምርመራ ውጤት ያገኙበትን ቀን ያስገቡ።
 • “Send Code (ኮድ ላክ)” የሚለውን ይምረጡ።

አይፎን፦

 • ወደ Settings (ቅንብሮች) ይሂዱ እና Exposure Notifications (የተጋላጭነት ማሳወቂያዎች)ይክፈቱ።
 • “Share a COVID-19 Diagnosis (የ COVID-19 ምርመራን ያጋሩ)" የሚለውን ይምረጡ።
 • “Continue” (“ቀጥል”) የሚለውን ከዚያ “Didn’t get a code? (“ኮድ አላገኙም?) የሚለውን ይምረጡ። የዋሺንግተን ግዛት የጤና መምሪያ ድር ጣቢያን ይጎብኙ።"
 • WA Notify የሚጠቀመውን መሳሪያዎን ስልክ ቁጥር እና አወንታዊ የ COVID-19 ምርመራ ውጤት ያገኙበትን ቀን ያስገቡ።
 • “Continue (ቀጥል)” የሚለውን ይምረጡ።

የማረጋገጫ ሊንክ ብቅ የሚል ማሳወቂያ እና የጽሁፍ መልእክት ይደርስዎታል። ማንነትዎን ሳያሳውቁ ሌሎች ተጠቃሚዎችን ሊከሰት ለሚችል ተጋላጭነት ለማንቃት ማሳወቂያን መንካት ወይም በጽሁፍ መልእክቱ ውስጥ ያለውን ሊንክ መጫን እና WA Notify ውስጥ ያሉ ደረጃዎችን መከተል ብቻ ያስፈልግዎታል። የእርስዎን አዎንታዊ ውጤት ሪፖርት ለ Department of Health (DOH፣ የጤና መምሪያ) ለማድረግ የማረጋገጫ ኮድዎን በ WA Notify ከጠየቁ በኋላ, ወደ ግዛቱ ኮቪድ-19 ነጻ የስልክ መስመር፣ በ 1-800-525-0127፣ ይደውሉ ከዚያም # ን ይንኩ።

በ WA Notify ውስጥ የማረጋገጫ ኮድ መጠየቅ ካልቻሉ የግዛቱን ኮቪድ-19 ነጻ የስልክ መስመር መደወል አለባችሁ፣  1-800-525-0127፣ በመቀጠል # ን ይጫኑ እና እርስዎ የ WA Notify ተጠቃሚ መሆንዎን ለቀጥታ መስመር ሰራተኞች ያሳውቁ።የቀጥታ የስልክ መስመሩ ሰራተኞች ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉ ሌሎች የ WA Notify ተጠቃሚዎችን እንዲያነቁ መጠቀም የሚችሉትን የማረጋገጫ ሊንክ ሊሰጡዎች ይችላሉ።

በቤት ውስጥ ምርመራ የተገኙ ፖዘቲቭ ውጤቶችን እንዴት ሪፖርት ያደርጋሉ

ያለ ማዘዣ የመመርመሪያ ኪቶችን የሚገዙ እና አወንታዊ ውጤት የሚያገኙ ሰዎች ውጤቶችን እንዳገኙ ወደ ግዛቱ ኮቪድ-19 ነጻ የስልክ መስመር በ፣ 1-800-525-0127 መደወል ከዚያ # ን (ለስፓኒሽ 7 ን መጫን) አለባቸው።ለቀጥታ መስመር ሰዓቶች የ Contact Us  ገጽን ይጎብኙ። የቋንቋ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።

እባክዎ ያስታውሱ፦WA Notify የተጋላጭነት ማሳወቂያ መሳሪያ ነው። ተጠቃሚዎች የምርመራ ውጤቶቻቸውን እንዲያስገቡ የተሰራ አይደለም።

ግላዊነቴ እንዴት ይጠበቃል?

WA Notify የተጠቃሚውን ግላዊነት ለመጠበቅ በተዘጋጀው በ Google Apple ተጋላጭነት ማሳወቂያ ቴክኖሎጂ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ማንኛውንም አካባቢ ወይም የግል መረጃ ሳይሰበስብ ወይም ሳይገልጽ ከበስተጀርባ ይሠራል ፣ እና ውጤታማ ሆኖ እንዲሰራ እርስዎ ማን እንደሆኑ ወይም የት እንዳሉ ማወቅ አያስፈልገውም። የብሉቱዝ ጥቃቅን ፍንዳታዎችን ብቻ በመጠቀም፣ የእርስዎ ባትሪ ምንም አይሆንም።

ተሳትፎዎ ሙሉ በሙሉ በፈቃደኝነት ነው። ተጠቃሚዎች በማንኛውም ጊዜ መርጠው መግባት ወይም መውጣት ይችላሉ። የተጠቃሚ ግላዊነት ጥበቃ እንዴት እንደሆነ የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ የ WA Exposure Notifications የግላዊነት ፖሊሲን ይመልከቱ።

ማሳወቂያዎቹ ምን ይመስላሉ?

ሊደርስዎት የሚችሉ ሁለት አይነት ማሳወቂያዎች አሉ። በምርመራ ፖዘቲቭ የሆኑት የማረጋገጫ ሊንክ የጽሁፍ መልእክት እና/ወይም ብቅ የሚል ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል። ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉ የ WA Notify ተጠቃሚዎች የተጋላጭነት ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል። ስለ እነዚህ ማሳወቂያዎች የበለጠ ይወቁ እና ምን እንደሚመስሉ ይመልከቱ

እንዴት ይረዳል?

በ University of Washington (እንግሊዘኛ ብቻ) በቅርብ ጊዜ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው የተጋላጭነት ማሳወቂያዎችን ሰዎች የበለጠ ሲጠቀሙ ጥቅሙ የበለጠ ይሆናል። ውጤቶች እንደሚያሳዩት WA Notify በግምት ከ 40 እስከ 115 ሰዎችን እንደታደገ እና ሥራ ላይ በነበረባቸው በመጀመሪያዎቹ አራት ወራት ውስጥ ወደ 5,500 ገደማ የሚሆኑ የኮቪድ -19 ጉዳዮችን መከላከል ችሏል። WA Notify የሚጠቀሙ ጥቂት ሰዎች እንኳን የ COVID-19 ኢንፌክሽኖችን እና ሞትን እንደሚቀንሱ የመረጃ ሞዴሎች ያሳያሉ፣ ይህም WA Notify የ COVID-19 ስርጭትን ለመከላከል ወሳኝ መሳሪያ እንደሆነ ያሳያል።

​ስለ WA Notify (WA ማሳወቂያ) መረጃ ማሰራጨት ይፈልጋሉ?

ለማህበራዊ ሚዲያ መልዕክቶች፣ ፖስተሮች፣ ለናሙና የሬዲዮ እና የቲቪ ማስታወቂያዎች የእኛን የ WA Notify የመገልገያ መሳሪያ ይመልከቱ።

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ሌሎች ጥያቄዎች

ከ Washington State Department of Health (DOH፣ የዋሺንግተን ግዛት የጤና መምሪያ) ማሳወቂያ እና/ወይም የጽሑፍ መልዕክት ደርሶኛል። ለምን?

DOH ለ COVID-19 ምርመራ በቅርቡ ፖዘቲቭ የሆኑ ሰዎች ለሚጠቀሙባቸው ስልክ ቁጥሮች የጽሁፍ መልእክት እና/ወይም ብቅ የሚል ማሳወቂያ ይልካል፣ ይህን የሚያደርገው የ WA Notify ተጠቃሚዎች ሊፈጠር ስለሚችል መጋለጥ በፍጠነት እና ማንነታቸውን ሳይገልጹ ለሌሎች ማሳወቅ እንዲችሉ ለማድረግ ነው። ስለ እነዚህ ማሳወቂያዎች የበለጠ ይወቁ እና ምን እንደሚመስሉ ይመልከቱ

ሁለቱም ከደረስዎት፣ ማንነትዎን ሳያሳውቁ ሌሎች ተጠቃሚዎችን ሊከሰት ለሚችል ተጋላጭነት ለማንቃት ማሳወቂያን መንካት ወይም በጽሁፍ መልእክቱ ውስጥ ያለውን ሊንክ መጫን እና WA Notify ውስጥ ያሉ ደረጃዎችን መከተል ብቻ ያስፈልግዎታል።

ተከትቤ ከነበረ WA Notify ያስፈልገኛል?

አዎ። ሙሉ ለሙሉ የ COVID-19 ክትባት ከወሰዱ በኋላም የተለመዱትን ጥንቃቄዎች መተግበር አለብዎት። እራስዎን ለመከላከል ክትባቶች ውጤታም መንገድ ናቸው፣ ነገር ግን ሊያዙ ወይም ሌሎች ያልተከተቡ ሰዎች እንዲያዙ ሊያደርጉ የሚችሉበት አነስተኛ ስጋት አለ።

የእኔን የ WA Notify ውሂብ ለሕዝብ ጤና ስለ ማበርከት የተመለከተ ማሳወቂያ ደርሶኛል። ለምን?

የ Washington State Department of Health (DOH) በመሣሪያው ላይ የሚያስፈልጉ ማሻሻያዎችን ማድረግ እንድንችል WA Notify ምን ያክል በጥሩ ሁኔታ እየሠራ እንዳለ ለማወቅ ይፈልጋል። የእርስዎን የ WA Notify ውሂብ እንድናጋራ የሚስማሙ ከሆነ፣ የእርስዎ ግላዊነት አሁንም ድረስ ቢሆን ሙሉ በሙሉ ጥበቃ የሚደረግለት ይሆናል። ምንም ዓይነት የግል መረጃ አይሰበሰብም ወይም ለሌሎች አይጋራም እንዲሁም እርስዎን ለይቶ ማወቅ የሚያስችል ምንም መንገድ የለም። DOH ብቻ ይህን ውሂብ በግዛት ደረጃ ብቻ ሊደርስበት ይችላል።

የ WA Notify ተጠቃሚዎች የእነርሱ ውሂብ እንዲጋራ ከተስማሙ፣ የሚሰበሰበው መረጃ ምንድን ነው?

የእርስዎ ውሂብ እንዲጋራ የሚስማሙ ከሆነ፣ የእርስዎ ግላዊነት አሁንም ድረስ ቢሆን ሙሉ በሙሉ ጥበቃ የሚደረግለት ይሆናል። ምንም ዓይነት የግል መረጃ አይሰበሰብም ወይም ለሌሎች አይጋራም በመሆኑም እርስዎን ለይቶ ማወቅ የሚያስችል ምንም መንገድ የለም። Washington State Department of Health  ብቻ ይህን በስቴት ደረጃ የወጣ ውሂብ ማየት የሚችል ሲሆን ይህም የሚከተሉትን ያካትታል፦

 • በእነርሱ WA Notify ውስጥ ያለው ውሂባቸው እንዲጋራ የተስማሙ ሰዎች ብዛት። ይህ የእኛ ናሙና ምን ያክል ሁሉንም ወካይ እንደሆነ እንድናውቅ ያስችለናል።
 • የ WA Notify ተጠቃሚዎች የተቀበሉት Exposure Notifications ብዛት። ይህ የ COVID-19 ስርጭትን አካሄድ እንድናይ ያግዘናል።
 • በተጋላጭነት ማሳወቂያ ላይ ጠቅ ያደረጉ ሰዎች ብዛት። ይህ ሰዎች ምን ያክል የሕዝብ ጤና ምክሮችን ለመስማት ፈቃደኛ እንደሆኑ እንድንረዳ ያግዘናል።

የ COVID-19 ምርመራ ውጤታቸው አዎንታዊ ከሆነ ሰው አጠገብ የነበሩ ሰዎች ሆኖም ግን ተጋላጭ እንደሆኑ ማሳወቂያ እንዳይላክላቸው ያን ያክል ያልተቀራረቡ ወይም ለረዥም ጊዜ ያልቆዩ ሰዎች ብዛት። ይህ በ WA Notify ያለው የተጋላጭነት ማሳወቂያ ቀመር መስተካከል እንዳለበት ወይም እንደሌለበት እንድንወስን ያግዘናል።

በእኔ iPhone ላይ WA Notify ን ሳሠራው፣ "Availability Alerts (የተገኝነት ማንቂያዎች)"ን ማብራት ወይም ማጥፋት አለብኝ?

ማጥፋት ችግር የለውም። ሆኖም ግን ከዋሽንግተን ግዛት ለረዥም ጊዜ ርቀው የሚጓዙ ከሆነ ቢያበሩት ይመከራል። የተገኝነት ማንቂያዎች ሲበሩ፣ WA Notify በሌለበት ቦታ በሚሆኑበት ጊዜ በዚያ ቦታ በሚሠራ ሌላ የተጋላጭነት ማሳወቂያ ቴክኖሎጂ አማካይነት ማሳወቂያ ሊደርስዎት ይችላል። iPhone ተጠቃሚዎች በርካታ ክልሎችን መጨመር ይችላሉ ሆኖም ግን በአንድ ጊዜ አንድ ብቻ ክልልን እንደሚገኙበት ቦታ መመደብ ይችላሉ። አዲስ ቦታ እንዲሠራ ለማድረግ ክልልን ማስወገድ አያስፈልግዎትም። የ Android ተጠቃሚዎች ከበርካታ ግዛቶች እንደ WA Notify ያሉ የተጋላጭነት ማሳወቂያ መተግበሪያዎችን መግጠም ይችላሉ ሆኖም ግን ከ WA Notify ጋር ስምሙ የሆነ ቴክኖሎጂ ብቻ በአንድ ጊዜ ንቁ ሆኖ መሥራት ይችላል።

WA Notify ለመጠቀም መርጬ መግባት አለብኝ?

አዎ። WA Notify ነፃ እና በፈቃደኝነት ነው። በማንኛውም ጊዜ መርጠው መውጣት ይችላሉ። በቀላሉ ባህሪውን ያጥፉ ወይም መተግበሪያውን ይሰርዙ። ስልኩ በአቅራቢያ ካሉ ሌሎች ተጠቃሚዎች ያከማቸው ሁሉም የዘፈቀደ ኮዶች ይሰረዛሉ እና መልሶ ማግኘት አይቻልም፡፡

WA Notify የእውቂያ ፍለጋ መተግበሪያ ነው?

አይደለም። WA Notify እርስዎ ስለሚገናኛቸው ሰዎች መረጃን አይከታተልም፣ ስለሆነም “የእውቂያ ፍለጋ” አያደርግም። እውቂያ ፍለጋ ለ COVID-19 ፖዘቲቭ የሆነን ወይም የተጋለጠን ማንኛውንም ሰው ይለያል። መተግበሪያው ማንኛውንም የግል መረጃ አይሰበስብም ወይም አይለዋወጥም፣ ስለሆነም ከማን ጋር እንደተገናኙ ማንም ማወቅ አይችልም።

"ተጋላጭነት" ምንድነው?

ለ COVID-19 አዎንታዊ ምርመራ ካደረገ ከሌላ የ WA Notify ተጠቃሚ አቅራቢያ ጉልህ ጊዜ ባሳለፉበት ጊዜ ተጋላጭነት ይከሰታል። ይህ የ COVID-19 አካላዊ ርቀትን እና ስርጭትን በተመለከተ የአሁኑን የ Centers for Disease Control and Prevention (CDC፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከላት) መመሪያን (እንግሊዘኛ ብቻ) ይከተላል። ተጋላጭነትን ለመወሰን፣ WA Notify ከ CDC የቅርብ ንክኪ ትርጉም ጋር የሚዛመድ አልጎሪዝም ይጠቀማል - በሚተላለፍበት ወቅት 6 ጫማ (2 ሜትር) ገደማ ለ 15 ደቂቃ ወይም ከዚያ በላይ – እና በሕዝብ ጤና ባለስልጣኖች ሊስተካከል ይችላል።

WA Notify ተጋላጭ እንደሆንኩ ቢነግረኝ ምን ይፈጠራል?

የ WA Notify እርስዎ የተጋለጡ ሊሆኑ እንደሚችሉ ካወቀ፣ በስልክዎ ላይ ያለው ማሳወቂያ ቀጥሎ ምን ማድረግ እንዳለብዎት መረጃ ወዳለው ድረ-ገጽ ይመራዎታል። ይህ እንዴት እና የት መመርመር እንዳለብዎት፣ እራስዎን እና በቅርብዎ ያሉትን ደህንነት ስለመጠበቅ መረጃ፣ እና ለጥያቄዎችዎ መልስ የሚሆኑ መርጃዎችን ያጠቃልላል። በድረ-ገጹ ላይ ያሉትን መመሪያዎች በጥንቃቄ ማንበብ እና መከተል አስፈላጊ ነው።

ለ COVID-19 አዎንታዊ ምርመራ ካደረግኩ ሰዎች ያውቃሉ?

አይ። WA Notify ስለ እርስዎ ማንኛውንም መረጃ ለማንም ሰው አያጋራም። አንድ ሰው የተጋላጭነት ማሳወቂያ ሲደርሰው፣ ባለፉት 14 ቀናት ውስጥ ቅርቡ የነበረ አንድ ሰው ለ COVID-19 አዎንታዊ ምርመራ ማድረጉን ብቻ ያውቃል። ግለሰቡ ማን እንደነበረ ወይም ተጋላጭነቱ የት እንደደረሰ አያውቁም።

ለ WA Notify መክፈል አለብኝ?

አይ። WA Notify ነፃ ነው።

WA Notify ለዋሽንግተን ግዛት እንዴት ይረዳል?

በ University of Washington (እንግሊዘኛ ብቻ) በቅርብ ጊዜ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው የተጋላጭነት ማሳወቂያዎችን ሰዎች የበለጠ ሲጠቀሙ ጥቅሙ የበለጠ ይሆናል። WA Notify ጥቅም ላይ በዋለባቸው የመጀመሪያዎቹ አራት ወራት ላይ በግምት ከ 40 እስከ 115 የሚሆኑ ሰዎችን ህይወት እንዳዳነ እና ወደ 5,500 አካባቢ የ COVID-19 ጉዳዮችን እንደተከላከለ ውጤቶች አሳይተዋል። WA Notify የሚጠቀሙ ጥቂት ሰዎች እንኳን የ COVID-19 ኢንፌክሽኖችን እና ሞትን እንደሚቀንሱ የመረጃ ሞዴሎች ያሳያሉ፣ ይህም WA Notify የ COVID-19 ስርጭትን ለመከላከል ወሳኝ መሳሪያ እንደሆነ ያሳያል።

ከግዛት ውጭ ከተጓዝኩ WA Notify ለስራዬ ያሳውቃል?

አዎ። የ Apple/Google ቴክኖሎጂን የሚጠቀም መተግበሪያ ወዳለው አንድ ግዛት የሚጓዙ ከሆነ፣ ስልክዎ በዚያ ግዛት ውስጥ ካሉ ተጠቃሚዎች ጋር የዘፈቀደ ኮዶችን መለዋወጥን ይቀጥላል። በመተግበሪያ ቅንብሮችዎ ውስጥ ማንኛውንም ነገር መለወጥ አያስፈልግም። ለተራዘመ ጊዜ ከዋሽንግተን ለቀው ከሄዱ፣ የአከባቢን ድጋፍ እና ማስጠንቀቂያ ለማግኘት በአዲሱ ግዛት ውስጥ ያሉትን አማራጮች መገምገም አለብዎት።

ለምን ሁለቱም የእውቂያ ፍለጋ እና WA Notify ያስፈልጉናል?

የግንኙነት ፍለጋ ለአስርተ ዓመታት ውጤታማ የህዝብ ጤና ጣልቃ ገብነት ሆኗል። WA Notify ይህንን ስራ በማይታወቅ መልኩ ይደግፋል። ምሳሌ ይኸውልዎት፦ ለ COVID-19 አዎንታዊ ምርመራ ካደረጉ፣ የሕዝብ ጤና ጥበቃ ባለሥልጣኖች ደውለው የቅርብ ጊዜ ቅርብ ግንኙነቶችዎን እንዲያጋሩ ሊጠይቁዎት ይችላሉ። በአውቶብስ ውስጥ አጠገቡ የተቀመጡትን እንግዳ ሰው ስም መጥቀስ አይችሉም። ሁለታችሁም WA Notify የምትጠቀሙ ከሆነ፣ አውቶቡሱ ውስጥ የነበረው እንግዳ ተጋላጭነት ሊኖረው እንደሚችል በስውር ማሳወቂያ ይደርሰዋል እናም COVID-19 ለጓደኞቻቸው እና ለቤተሰቦቻቸው እንዳይዛመት ለመከላከል እርምጃዎችን መውሰድ ይችላሉ። ልክ እንደ እጅ መታጠብ እና የፊት መሸፈኛ ጭምብል እንደማድረግ እያንዳንዱ COVID-19 እንዳይስፋፋ ይረዳል፣ አንድ ላይ ደግሞ የበለጠ ውጤታማ ናቸው።

WA Notify ለሌሎች ተጠቃሚዎች ለማሳወቅ ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?

በሌላ ተጠቃሚ ለ COVID-19 የተጋለጡ ሊሆኑ የሚችሉ ተጠቃሚዎች COVID-ያለበት/የያዘው ተጠቃሚ ሌሎችን የ WA Notify ተጠቃሚዎች ማንነትን ሳይገልጽ ለማሳወቅ በ WA Notify ውስጥ ያሉትን ቅደም ተከተሎች ከተከተለ በኋላ በ 24 ሰዓታት ውስጥ ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል።

ከ WA Notify ብዙ ማስጠንቀቂያዎችን መቀበል ይቻላል?

በሌላ ተጠቃሚ ለ COVID-19 የተጋለጡ ሊሆኑ የሚችሉ ተጠቃሚዎች COVID-ያለበት/የያዘው ተጠቃሚ ሌሎችን የ WA Notify ተጠቃሚዎች ማንነትን ሳይገልጽ ለማሳወቅ በ WA Notify ውስጥ ያሉትን ቅደም ተከተሎች ከተከተለ በኋላ በ 24 ሰዓታት ውስጥ ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል።

ለ COVID አዎንታዊ ምርመራ ካደረግኩ ለ WA Notify እንዴት መናገር እችላለሁ?

አዎንታዊ ምርመራ ካደረጉ እና ከ Washington State Department of Health (DOH፣ የዋሽንግተን ግዛት ጤና መምሪያ) ወይም የአካባቢዎ የህዝብ ጤና ባለስልጣን የሆነ ሰው WA Notify ን እየተጠቀሙ መሆንዎን ይጠይቅዎታል።የሚጠቀሙ ከሆነ፣ የማረጋገጫ አያያዥ እና/ወይም ማሳወቂያ ይልኩልዎት እና ወደ WA Notify ለመግባት ቅደም ተከተሎቹን እንዲከተሉ ይረዱዎታል። አያያዡ ወይም ማሳወቂያው ከግል መረጃዎ ጋር የተያያዘ አይደለም። ቅደም ተከተሎቹን ሲከተሉ ስለ ተጋላጭነታቸው በመተግበሪያው በኩል ማን ማሳወቂያ እንደሚደርሰው DOH  የሚያውቅበት መንገድ የለውም። የተጋላጭነት ማሳወቂያው ስለ እርስዎ፣ ወይም የት በአቅራቢያዎ እንደነበሩ መረጃን አያካትትም። በ WA Notify በኩል ማንነታቸውን ሳይገልጹ ውጤቶቻቸውን የሚያረጋግጡ ሰዎች በጨመሩ ቁጥር፣ የ COVID-19 ስርጭትን በተሻለ ሁኔታ ልንከላከል እንችላለን።

አዎንታዊ ምርመራ ካደረጉ እና አሁንም ስም ሳይገለጽ ውጤትዎን በ WA Notify ማረጋገጥ ካለብዎት፣ ለሌሎች ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉ WA Notify ተጠቃሚዎችን ለማሳወቅ የማረጋገጫ ኮድ ለመጠየቅ የዚህን ገጽ ክፍል “How to request a verification code for positive at-home COVID-19 test results (ለቤት ውስጥ የ COVID-19 አወንታዊ ምርመራ ውጤት የማረጋገጫ ኮድ እንዴት እንደሚጠየቅ)" ይመልከቱ።

የእርስዎን አዎንታዊ ውጤት ሪፖርት ለ Department of Health (DOH፣ የጤና መምሪያ) ለማድረግ የማረጋገጫ ኮድዎን በ WA Notify ከጠየቁ በኋላ፣ ወደ ግዛቱ ኮቪድ-19 ነጻ የስልክ መስመር፣ በ 1-800-525-0127፣ ይደውሉ ከዚያም # ን ይንኩ።

WA Notify ን ወደ ስልኬ ካከልኩ በኋላ ማድረግ ያለብኝ ነገር አለ?

ተጨማሪ እርምጃ የሚያስፈልግው የሚከተሉት ከሆኑ ብቻ ነው፦

 1. ለ COVID-19 አዎንታዊ ምርመራ ካደረጉ፣ ወይም
 2. ተጋልጠው ሊሆን እንደሚችል ማሳወቂያ ከደረስዎት ነው።

አዎንታዊ ምርመራ ካደረጉ  እና ከWashington State Department of Health (DOH፣ የዋሽንግተን ግዛት ጤና መምሪያ) ወይም የአካባቢዎ የህዝብ ጤና ባለስልጣን የሆነ ሰው  WA Notifyን እየተጠቀሙ መሆንዎን ይጠይቅዎታል።የሚጠቀሙ ከሆነ፣ የማረጋገጫ አያያዥ እና/ወይም ማሳወቂያ ይልኩልዎት እና ወደ WA Notify ለመግባት ቅደም ተከተሎቹን እንዲከተሉ ይረዱዎታል። አያያዡ ወይም ማሳወቂያው ከግል መረጃዎ ጋር የተያያዘ አይደለም። ስለ ተጋላጭነታቸው በመተግበሪያው በኩል ማን ማሳወቂያ እንደሚደርሰው DOH  የሚያውቅበት መንገድ የለውም። የተጋላጭነት ማሳወቂያው ስለ እርስዎ፣ ወይም የት በአቅራቢያዎ እንደነበሩ መረጃን አያካትትም። በ WA Notify በኩል ማንነታቸውን ሳይገልጹ ውጤቶቻቸውን የሚያረጋግጡ ሰዎች በጨመሩ ቁጥር፣ የ COVID-19 ስርጭትን በተሻለ ሁኔታ ልንከላከል እንችላለን።

አዎንታዊ ምርመራ ካደረጉ እና የማረጋገጫ ኮድ ካስፈለግዎት፣ ለሌሎች ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉ WA Notify ተጠቃሚዎችን ለማሳወቅ የማረጋገጫ ኮድ ለመጠየቅ የዚህን ገጽ ክፍል  “How to request a verification code for positive at-home COVID-19 test results (ለቤት ውስጥ ለኮቪድ-19 አወንታዊ ምርመራ ውጤት የማረጋገጫ ኮድ እንዴት እንደሚጠየቅ) ይመልከቱ።

የእርስዎን አዎንታዊ ውጤት ሪፖርት ለ Department of Health (DOH፣ የጤና መምሪያ) ለማድረግ የማረጋገጫ ኮድዎን በ WA Notify ከጠየቁ በኋላ፣ ወደ ግዛቱ ኮቪድ-19 ነጻ የስልክ መስመር፣ በ 1-800-525-0127፣ ይደውሉ ከዚያም # ን ይንኩ።

የ WA Notify እርስዎ የተጋለጡ ሊሆኑ እንደሚችሉ ካወቀ፣ በስልክዎ ላይ ያለው ማሳወቂያ ቀጥሎ ምን ማድረግ እንዳለብዎት መረጃ ወዳለው ድረ-ገጽ ይመራዎታል። ይህ እንዴት እና የት መመርመር እንዳለብዎት፣ እራስዎን እና በቅርብዎ ያሉትን ደህንነት ስለመጠበቅ መረጃ፣ እና ለጥያቄዎችዎ መልስ የሚሆኑ መርጃዎችን ያጠቃልላል። በድረ-ገጹ ላይ ያሉትን መመሪያዎች በጥንቃቄ ማንበብ እና መከተል አስፈላጊ ነው። ማሳወቂያው ማን አጋልጥዎት ሊሆን እንደሚችል እና የት እንደሆነ መረጃን አያካትትም። እሱ ሙሉ በሙሉ የማይታወቅ ነው።

WA Notify መጠቀም ባትሪዬን ይጨርሳል ወይም ብዙ ዳታ ይጠቀማል?

አይ። Bluetooth Low Energy technology በመጠቀም በዳታዎ እና በባትሪዎ ህይወት ላይ አነስተኛ ውጤት እንዲኖረው ተደርጎ የተሰራ ነው።

WA Notify እንዲሰራ ብሉቱዝ በርቶ እንዲቆይ ማድረግ ያስፈልገኛል?

አዎ። WA Notify Bluetooth Low Energy ይጠቀማል፣ ስለሆነም ብሉቱዝ በአቅራቢያ ያሉ ሌሎች ተጠቃሚዎችን ለመለየት ሲስተሙ ሁል ጊዜ መብራት አለበት።

ስልኬ ላይ እንዲሰራ WA Notify መክፈት ያስፈልገኛል?

አይ። WA Notify ከበስተጀርባ ይሠራል።

WA Notify ቆየት ባሉ ስማርት ስልኮች ላይ ሊሠራ ይችላል?

iPhone ተጠቃሚዎች የእርስዎ ሥርዓተ ክወና እንደሚከተለው ከሆነ WA Notify ን መጠቀም ይችላሉ፦

 • iOS ስሪት 13.7 ወይም ከዚህ በኋላ የመጣ (ለ iPhone 6s፣ 6s Plus፣ SE ወይም የተሻለ አዲስ)

 • iOS ስሪት 12.5 (ለ iPhone 6፣ 6 plus፣ 5s)

የ Android ተጠቃሚዎች የእርስዎ Android ስማርት ስልክ ብሉቱዝ ዝቅተኛ ኃይል አጠቃቀምን የሚቀበል ከሆነ እና Android ስሪት 6 (API 23) ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ WA Notify ን መጠቀም ይችላሉ።

WA Notify ለመጠቀም 18 ዓመት መሆን አለብኝ?

አይ። WA Notify ዕድሜዎን አያውቅም ወይም አይፈትሽም።

ስልኩን ከአንድ ሰው ጋር ከተጋራሁ ይህ ቴክኖሎጂ ይሠራል?

WA Notify በተጋላጭነት ጊዜ ስልኩን ማን ሲጠቀምበት እንደነበረ ማወቅ አይችልም፡፡ ስልክ የሚያጋሩ ከሆነ፣ WA Notify ለ COVID-19 ተጋላጭነትን የሚያመለክት ከሆነ ስልኩን የሚጠቀም እያንዳንዱ ሰው የህዝብ ጤና መመሪያዎችን መከተል አለበት፡፡

WA Notify እንደ iPads ወይም ስማርት ሰዓቶች ባሉ መሣሪያዎች ላይ ሥራውን ያሳውቃል?

አይ። የተጋላጭነት ማሳወቂያ ማዕቀፍ በተለይ ለስማርት ስልኮች የተዠጛጀ ሲሆን በአይፓዶች ወይም ታብሌቶች ላይ አይደገፍም/አይሰራም፡፡

ስማርት ስልኮች ለሌላቸው ሰዎች የዋሽንግተን ግዛት ለዚህ ቴክኖሎጂ ተደራሽነት ምን እያደረገ ነው?

WA Notify የ COVID-19 ስርጭትን ለመከላከል የሚረዳ ብቸኛው መሳሪያ አይደለም፡፡ የእውቂያ ፍለጋ/ፈለግ እና ሌሎች ጥረቶች ስማርት ስልክ ባይኖራቸውም ለእያንዳንዱ የዋሺንግተንን ነዋሪ ይጠቅማሉ፡፡ ክትባቶች የ COVID-19 ስርጭትን ለመከላከል ምርጥ መንገዶች ናቸው፣ የፊት መሸፈኛ ጭምብሎችን ማድረግ፣ አካላዊ ረቀት እና የስብሰባዎችን መጠን መገደብ ሁሉም ሰው ሊያደርጋቸው የሚችል የ COVID-19 ስርጭትን ለማስቆም የሚረዱ ሌሎች መንገዶች ናቸው።

የፌዴራል መንግሥት Lifeline program (የሕይወት መስመር መርሃ-ግብር) ብቁ ለሆኑ ሰዎች ወርሃዊ የስልክ ሂሳብ ብድር ይሰጣል። አንዳንድ ተሳታፊ የገመድ አልባ አገልግሎት አቅራቢዎች ነፃ ስማርትፎንም ሊሰጡ ይችላሉ። ስለ መርሃ-ግብሩ፣ ማን ብቁ እንደሆነ፣ እንዴት ማመልከት እና መሳተፍ እንደሚቻል እና ተሳታፊ የገመድ አልባ አገልግሎት አቅራቢዎች የበለጠ ይወቁ (እንግሊዘኛ ብቻ)።

ያስታውሱ፣ የ COVID-19 ን ክትባት መውሰድ ስርጭቱን ለማስቆም ከሁሉ የተሻለ ምርጡ መንገድ ነው።

WA Notify በጣም ብዙ ባትሪ እየተጠቀመ ያለ የሚመስለው ለምንድን ነው?

ለነገሩ፣ ባትሪ አይፈጅም። እንደ WA Notify ያሉ መተግበሪያዎችን ጨምሮ የእርስዎ ባትሪ በየቀኑ ምን ያክል ጥቅም ላይ እንደዋለ የሚያሳይ መቶኛን በእርስዎ መሣሪያ ላይ ያለው የባትሪ አጠቃቀም ያሳያል። አብዛኛዎቹ መተግበሪያዎች ሌሊቱን ሙሉ አይሠሩም። WA Notify ቢሆንም አይሠራም፣ ሆኖም ግን ምናልባት ተጋላጭነት ካለ ለእርስዎ እንዲያስጠነቅቅዎት በየተወሰነ ሰዓት ልዩነት በዘፈቀደ የተወሰኑ ኮዶችን ለማረጋገጥ ፍተሻ ያደርጋል። ስለዚህ፣ ለምሳሌ እርስዎ ተኝተው እያለ ሌሎች መተግበሪያዎች የማይሠሩ ያለ ከሆነ፣ WA Notify በዚህ ጊዜ ላይ ከፍተኛ የሆነውን የባትሪ አጠቃቀም መቶኛ ድርሻ ሊወስድ ይችላል። ይህ ማለት ግን WA Notify በጣም ብዙ ባትሪ እየፈጀ ነው ማለት አይደለም - ጥቅም ላይ ከዋለው አነስተኛ የባትሪ ፍጆታ ላይ ከፍተኛው መቶኛ ደርሶታል ማለት ነው።

ዋሽንግተን WA Notify ን በ 30 ቋንቋዎችን ለቆ ነበረ፣ እና ታዲያ ለምን በ Google Play መደብር ውስጥ በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽኛ እንደቀረበ ብቻ ሆኖ ይታየኛል?

WA Notify በተጠቃሚው ስልክ እንደ ዋና ቋንቋ ሆኖ በተቀናበረው ቋንቋ ብቻ ይሠራል። አንድ ብቻ የ WA Notify ስሪት አለ፣ ሆኖም ማናቸውም ብቅ ባይ ማሳወቂያዎች - የተጋላጭነት ማሳወቂያ ለምሳሌ - ዋሽንግተን ግዛት ካቀረባቸው 30 ቋንቋዎች መካከል በተጠቃሚው ተመራጭ ቋንቋ አማካይነት የሚታዩ ይሆናሉ። 

ማሳወቂያ እና/ወይም የጽሁፍ መልእክት ደርሶኛል ነገር ግን የተመረመረው ሰው የቤተሰብ ወይም የቤት አባል ነበር። ምን ማድረግ አለብኝ? 

ፖዘቲቭ የሆነ የ WA Notify ተጠቃሚ ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉ ሌሎች ሰዎችን ማንነቱ ሳይታወቅ ለማንቃት ደረጃዎችን መከተል አለበት፣ ስለዚህ ለእርስዎ ያልሆኑ ማንኛውንም መልእክቶች ወይም ማሳወቂያዎች ችላ ማለት አለብዎት።

የእርስዎ ቤተሰብ ወይም የቤተሰብ አባል የ WA Notify ተጠቃሚ ከሆነ፣ ፖዘቲቭ ውጠት ካለው፣ እና አሁንም ውጠቱን በ WA Notify ማረጋገጥ ካለበት፣ በዚህ ገጽ ላይ “How to request a verification code for positive at-home COVID-19 test results "በቤት ውስጥ ለ COVID-19 አወንታዊ የማረጋገጫ ኮድ እንዴት እንደሚጠየቁ ቅደም ተከተሎችን መከተል ይችላሉ" ላይ የተጠቀሱትን ቅደም ተከተሎች መከተል ይሽላል።

ያለ ማዘዣ የመመርመሪያ ኪቶችን የሚገዙ እና አወንታዊ ውጤት የሚያገኙ ሰዎች ውጤቶችን እንዳገኙ ወደ ግዛቱ COVID-19 ነጻ የስልክ መስመር በ፣ 1-800-525-0127 መደወል ከዚያ # ን (ለስፓኒሽ 7 ን መጫን) አለባቸው። ለቀጥታ መስመር ሰዓቶች የ Contact Us (አግኙን) ገጽን ይጎብኙ። የቋንቋ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።

ማሳወቂያውን ለመንካት ወይም የማረጋገጫ ሊንኩን ለማንቃት ምን ያክል ጊዜ አለኝ?

WA Notify ውስጥ ሌሎችን ለማሳወቅ እርምጃዎቹን ለመከተል ማሳወቂያው ወይም የጽሁፍ መልእክት ከደረሰዎት በኋላ 24 ሰአት አልዎት። በዚያ ጊዜ ውስጥ ማሳወቂያውን መንካት ካልቻሉ ወይም የማረጋገጫ አገናኙን ጠቅ ማድረግ ካልቻሉ፣ የዚህ ገጽ ክፍል "How to request a verification code for positive at-home COVID-19 test results (በቤት ውስጥ ለኮቪድ-19 አወንታዊ ምርመራ ውጤት የማረጋገጫ ኮድ እንዴት እንደሚጠየቅ)” ላይ ያሉትን ቅደም ተከተሎች በመከተል የማረጋገጫ ኮድ በWA Notify መጠየቅ ይችላሉ።የእርስዎን አዎንታዊ ውጤት ለ DOH (የጤና መምሪያ) ሪፖርት ለማድረግ COVID-19፣ የማረጋገጫ ኮድዎን በ WA Notify ከጠየቁ በኋላ ወደ ግዛቱ COVID-19 ነጻ የስልክ መስመር፣ በ 1-800-525-0127፣ ይደውሉ ከዚያም # ን ይንኩ። እንዲሁም አንድ ሰው ከ DOH ወይም ከአከባቢዎ የጤና ባለስልጣን ስለ የ COVID-19 ምርመራ ውጤት ሲያነጋግርዎት አያያዥ መጠየቅ ይችላሉ።

ዋሽንግተን ይህንን መፍትሄ ለምን መረጠ?

ዋሽንግተን የ Apple/Google መፍትሄን ለመገምገም የደህንነት እና የዜጎች ነፃነት ባለሙያዎችን እና የበርካታ ማህበረሰቦችን አባላትን ጨምሮ የመንግስት ቁጥጥር ቡድን አቋቋመ፡፡ ቡድኑ በመድረኩ በተረጋገጠው አስተማማኝነት ፣ ጠንካራ የመረጃ ጥበቃ እና በሌሎች ግዛቶች አጠቃቀም ላይ በመመርኮዝ ጉዲፈቻን መክሯል/እንደ ሃሳብ አቅርቧል፡፡

በ WA Notify ላይ ተጋላጭ ልሆን የቻልኩበትን ቀን እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

በ iPhone ላይ፦

 1. ወደ Settings (ቅንብሮች) ይሂዱ
 2. የ Exposure Notifications (የተጋላጭነት ማሳወቂያዎች) ይምረጡ ወይም Exposure Notifications (የተጋላጭነት ማሳወቂያዎች) በመፈለጊያው ላይ ያስገቡ
 3. ተጋላጭ ሊሆኑበት የቻሉት ቀን በ “You may have been exposed to COVID-19 (ለ COVID-19 ተጋልጠው ሊሆኑ ይችላል)” ስር የሚታይ ይሆናል

በ Android ላይ፦

 1. የ WA Notify መተግበሪያን ይክፈቱ
 2. እባክዎን በ “ሪፖርት የተደረጉ የመጋለጥ ዕድሎች (Possible exposure reported)” ስር See Details (ዝርዝሮችን ይመልከቱ) የሚለውን ይምረጡ
 3. ተጋላጭ ሊሆኑበት የቻሉት ቀን በ “Possible Exposure Date (ተጋላጭ ሊሆኑ የቻሉበት ቀን)” ስር የሚታይ ይሆናል
ከ ንብረት ጋር የተያያዙ የሰራ ቅጥሮች እና ንግዶች

የስራ አጥ ጥቅማጥቅም

ሥራዎን ካጡ, ለሥራ አጥነት ክፍያ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ለሥራ አጥነት ክፍያ ጥያቄ እንዴት እንደሚሞሉ መረጃ ከፈለጉ ፣ ወደ 1-800-318-6022 ይደውሉ፡፡ ምላሽ ሲይገኙ፣ ቋንቋዎን በመንገር የ ትርጉም አገልግሎት ያግኙ፡፡

ሰራተኛና አሰሪ

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በእኛ ግዛት ውስጥ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞችን እና አሰሪዎችን ይነካል፡፡

የሰራተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ, ሰራተኞች ማድረግ ያለባቸው ነገሮች፡

 • ሰራተኞችን ስለ ኮቪድ-19 ምልክቶች በሚገባቸው ቋንቋ ማስተማር፡፡
 • የሰውነት መራራቀን ማጎልበት፡፡
 • ተከታታይ ን ህና መጠበቅ፡፡
 • በተደጋጋሚ እጅን በደንብ መታጠብ፡፡
 • የታመሙ ሰራተኞች በቤት እንዲቆዩ ማድረግ፡፡

ስለ የተከፈለ የህመም ፈቃድ፣ የሰራተኞች ካሳ እና የስራ ቦታ ደህንነት መስፈርቶች ማጠቃለያ በተመለከተ ለተለመዱ ጥያቄዎች መልሶች Department of Labor & Industries (ከሰራተኛ እና ኢንዱስትሪዎች ክፍል) በብዙ ቋንቋዎች ይገኛሉ።

ስለ ስራ ቦታዎ ደህንነት ስጋት ካሎት, ቅሬታዎን ለስራተኛ እና ኢንደስትሪ በዚህ ስልክ ቁጥር 800-423-7233 ያሳውቁ፡፡ የ ስልክ ትርጉም አገልግሎት ዝግጁ እንዲሆን ማድረግ፡፡

ሰለ ንግዶ እና ሰራተኞች ማንኛውም ጥያቄ ካሎት በዚህ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጊዜ, የሰራተኞች ደህንነት ዲፓርትመንትን በ 855-829-9243 በመደወል ያሳውቁ፡፡

የጤና ጥበቃና የጤና ኢንሹራንስ

ነጻ ወይንም በትንሽ ክፍያ የህክምና አገልግሎት መስጠት፡፡ የ ህክምና አገልግሎት ለማግኘት በዚህ ስልክ ይደውሉ 1-855-923-4633፡፡ ምላሽ ሲያገኙ, ቃንቅዎን በመንገር የ ትርጉም አገልግሎት ያግኙ፡፡

የውጭ ዜጎች የድንገተኛ ጊዜ ህክምና (ኤኤምአር) ሽፋን ብቁ የህክምና ድንገተኛ ሁኔታ ላጋጠማቸው እና የዜግነት ወይም የኢሚግሬሽን መስፈርቶችን የማያሟሉ ወይም ብቃት ያለው ግለሰብ ወይም የ 5-ዓመቱን ባር የማያሟላ ብቃት ያለው ፕሮግራም ነው፡፡

የዋሽንግተን የስልክ መስመርን በ1-800-322-2588 በመደወል ማግኘት ያለብዎትን የተለያዩ የጤና ፕሮግራሞችን እና አገልግሎቶችን ለመለየት እና ለማመልከት ይረዳዎታል፡፡ ይህ የሚያጠቃልለው፡

 • (ሴቶች, ጨቅላ ልጆቸ & ልጆች የምግብ ፕሮግራም)
 • የህክምና ኢንሹራንስ ለልጆች, እርጉዝ ሴቶች እና አዋቂዎቸ
 • የእርግዝና መቆጣጠሪያ በቴክ ቻርጅ ፕሮግራም
 • የጤናና የቤተሰብ ቁጥጥር ክሊኒክ
 • የርግዝናና ህ ናት መገልገያ እቃዎች
 • የጡት ማጥባት አገልግሎተ
 • በተጨማሪም የምግብ አገልግሎት አላቸው፡፡
የኢምግሬሽን እና ስደተኞች መረጃ

Office of Immigrant and Refugee Affairs (OIRA) ስደተኞች ስለ COVID-19 እና ስለ ስደተኛ ስጋቶች አስፈላጊ እውነታዎችን እንዲረዱ ያግዛቸዋል

 • ሆስፒታሎች እና ክሊኒኮች የዜግነት ወይም የኢሚግሬሽን ሁኔታን ከ ICE ጋር እንዲጋሩ አልተፈቀደላቸውም፡፡
 • ለኮቪድ-19 ምርመራ መደረግ እና ለበጎ አድራጎት ወይም ቅናሽ የሚደረግ የሕክምና እንክብካቤ ማግኘት ለአረንጓዴ ካርድ ወይም ለዜግነት ለማመልከት እድሎን አይጎዳውም፡፡
 • ለሥራ አጥነት ክፍያ ለማመልከት ትክክለኛ የማህበራዊ ዋስትና ቁጥር ያስፈልግዎታል፡፡ የሥራ አጥነት ጥቅማጥቅሞችን ለማግኘት ከአንድ ሰው ጋር መነጋገር ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 1-800-318-6022 ይደውሉ፡፡
 • የሥራ አጥነት ጥቅማጥቅሞችን መቀበል በሕዝብ ቻርጅ ሕግጋት መሠረት አረንጓዴ ካርድዎን ወይም ዜግነትዎን አያሳጣም፡፡
 • በኮቪድ-19 የታመመውን ሰው ለመንከባከብ ወይም እራስዎን ለመንከባከብ የዋሽንግተን ስቴት ቤተሰብ ለማስታመም የሚከፈልበት እና የህክምና ፈቃድ ለማግኘት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ይህንን ጥቅም ለማግኘት የማኅበራዊ ዋስትና ቁጥር አያስፈልግዎትም፡፡ ESD የተለያየ አይነት ሰነዶች ይቀበላል፡
 • እርዳታ የሚፈልጉ የንግድ ባለቤት ከሆኑ፣ ከፌዴራል አነስተኛ ንግድ አስተዳደር (Federal Small Business Administration) ለአስቸኳይ ብድር ማመልከት የነዋሪ ካርድ ወይም ዜግነት የማግኘት ችሎታዎን አደጋ ላይ አይጥልም።

The Office of Immigrant and Refugee Affairs (OIRA) ያለዎት ሁኔታ ወይም የቤተሰብ አባል ወይም የእርስዎ ጥቅሞችዎ ላይ እርግጠኛ ካልሆኑ፣ የስደተኞች ጠበቃ፣ የኢሚግሬሽን ኦፊሰር ወይም በ Department of Justice (DOJ) እውቅና የተሰጠው ተወካይ እንዲያነጋግሩ ይመክራል። በአሜሪካ የኢሚግሬሽን ጠበቆች ማህበር (American Immigration Lawyers Association) በኩል ጠበቃ ማግኘት ይችሉ ይሆናል ወይም በ DOJ-እውቅና የተሰጠው የድርጅት ድርገፅን መጎብኘት ይችላሉ።

OIRA ስደተኞችንና ተፈናቃዮችን ለመደገፍ ፕሮግራም አላቸው፡

 • የሰራ ፍለጋ እና ስልጠና፡፡
 • የኢሚግሬሽን ድጋፍ።
 • የወጣቶች ስልጠና፡፡
 • ለስደተኛ የእድሜ ባላጸጎች ፣ ለልጆች ፣ ለተማሪዎች እና ለሌሎች ድጋፍ ማድረግ፡፡፣
 • መደበኛ ፕሮግራሞች በ ኮቪድ-19 ወቅት በርቀት ክፍት ይሆናሉ። ጽ / ቤቱ ለስራ ወይም ለስራ አጥነት ለማመልከት ትምህርትዎን ለመደገፍ እና የመኖሪያ ቤት ድጋፍ ለመስጠት አዲስ አገልግሎቶች አሉት፡፡ የስደተኞች ጥሬ ገንዘብ ድጋፍ እና የስደተኞች የህክምና ድጋፍ ብቁነት እስከ ሴፕቴምበር 30 ቀን 2020 ድረስ ተራዝሟል።
 • ለአገልግሎቶች እና ለተጨማሪ መረጃ, በዚህ ስልክ 360-890-0691፡፡

ስለ ስደተኛ መብቶች ጥያቄዎች ፣ በቁጥጥር ስር ላሉ ዘመዶች / ጓደኞች ድጋፍ ለማግኘት እና ሌሎች ተዛማጅ መረጃዎች ፣ማግኘት ይችላሉ የዋሺንግተን ስደተኞች አንድነት ኔትዎርክ የስልክ መስመር 1-844-724-3737፡፡ የ ስልክ ትርጉም አገልግሎት ዝግጁ እንዲሆን ማድረግ፡፡

የአእምሮ እና ስሜታዊ(Emotional) ጤና

ይህ አስጨናቂ ጊዜ ሊሆን ይችላል። እርስዎ ወይም የምትወዳቸው ሰዎች ጭንቀት ፣ ኃዘን ፣ ፍርሃት ወይም ቁጣ መሰማት የ ተለመደ ነገር ነው፡፡ አንተ ብቻህን አይደለህም፡፡ እርዳታ መጠየቅ ምንም ችግር የለውም፡፡

ለ ጭንቀት እና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሁሉም ሰው ምላሽ የሚሰጥበት መንገድ ይለያያል፡፡ ማድረግ የሚችሉት በጣም አስፈላጊው ነገር እራስዎን ፣ ቤተሰብዎን እና ማህበረሰብዎን በተቻለ መጠን መንከባከብ ነው፡፡

አስቸጋሪ በሆኑ ጊዜያት ለመቋቋም ምን ይረዳዎታል? ከጓደኞችዎ እና ከቤተሰብዎ ጋር ተገናኝተዋል? ምናልባት በ ጥልቀት መተንፈስ እና ማፍታታት ፣ የተወሰነ የ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ወይም ጥሩ እንቅልፍ አግኝተዋል? ለራስ-እንክብካቤ ጊዜን ቅድሚያ መስጠት ውጥረትን ለመቀነስ ሊረዳ ይችላል፡፡

Washington Listensንን በዚህ ስልክ ይደውሉ 1-833-681-0211፡፡ የ ስልክ ትርጉም አገልግሎት ዝግጁ እንዲሆን ማድረግ፡፡ ለ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽ ፣ ዋሽንግተን Washington Listens የተባለ የድጋፍ መርሐ ግብር ይፋ አደረገች፡፡ Washington Listens አገልግሎቶችን የሚጠቀሙ ሰዎች ጭንቀትን ለመቆጣጠር እና በ ኮቪድ-19 የ ተነሳ ለውጦችን ለመቋቋም ድጋፍ ያገኛሉ፡፡ Washington Listens በዋሽንግተን ውስጥ ላለ ማንኛውም ሰው የ ድጋፍ ባለሙያን ለማነጋገር ይገኛል፡፡ ደዋዮች በአካባቢያቸው ካሉ የማኅበረሰብ ሀብቶች ድጋፍ እና ግንኙነትን ይቀበላሉ። ፕሮግራሙ ምስጢራዊ ነው፡፡

ችግር ከገጠምዎ እና ምክርን ለማግኘት ሰውን ማነጋገር ከፈለጉ ጥቂት አማራጮች አሉ፡፡

 • The Disaster Distress መስመር የስሜት መረበሽ ላጋጠማቸው ሰዎች አስቸኳይ የምክር አገልግሎት ይሰጣል ጭንቀት ከማንኛውም ተፈጥሮአዊ ወይም ከሰው ሰራሽ ጋር የተዛመደጭንቀት በዚህ ስልክ ይደውሉ 1-800-985-5990፡፡ ምላሽ ሲያገኙ, ቋንቋዎን በመንገር የ ትርጉም አገልግሎት ያግኙ፡፡ የእገዛ መስመሩ በየቀኑ ለ 24 ሰዓታት ይገኛል፡፡
 • ቀውስ ግንኙነቶች በስሜት ቀውስ ውስጥ ላሉት ግለሰቦች ፣ ቤተሰቦች እና ጓደኞች ፈጣን እርዳታ የሚሰጥ የ 24 ሰዓት ችግር መስመር አለው። በኪንግ ካውንቲ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ያገለግላል፡፡ የ ስልክ ትርጉም አገልግሎት ዝግጁ እንዲሆን ማድረግ፡፡ በዚህ ስልክ ይደውሉ 1-866-427-4747.
 • ብሔራዊ የራስን ሕይወት የመከላከል አነቃቂነት ራስን ስለ ማጥፋት ለሚያሰቡ ሰዎች የመከላከል እና የመፍትሄ ሃሳብ ያቀርባል፡፡ የሚወዷቸውን ሰዎች ቤተሰቦቻቸውን እና ጓደኞቻቸውን የሚረዱ መፍትሄ ለማግኘት የህይወት መስመሩን መደወል ይችላሉ። በዚህ ስልክ ይደውሉ 1-800-273-8255. ይህ የስልክ መስመር በቀን ለ 24 ሰዓታት በሳምንት 7 ቀናት ይገኛል፡፡ ለነባር ወታደሮች የተወሰነ የእገዛ መስመር አለ፡፡ በዚህ ስልክ ይደውሉ 1-800-273-8255 ወይም 1ን ይጫኑ. እርስዎ መስማት የተሳኖት እና የመስማት ችግር ካለብዎ, በዚህ ስልክ ይደውሉ 1-800-799-4889.
የምግብ ምንጮች

18 ዓመት ወይም ከዚያ በታች የሆነ ልጅ ካለዎት ከት / ቤቶች ነፃ ምግብ ሊያገኙ ይችላሉ። በትምህርት ፕሮግራሞች ውስጥ የተመዘገቡ የአካል ጉዳተኞች አዋቂዎችም ለት / ቤት ምግብ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በአብዛኛዎቹ አጋጣሚዎች እነዚህ ምግቦች እንደ አውቶቡስ ማቆሚያዎች ባሉ በትምህርት ቤት እና አቅራቢያ አካባቢዎች ይሰጣሉ። ነፃ ምግብ የሚሰጡ ከሆነ ለማወቅ የትምህርት ቤቱን ወረዳዎን ያነጋግሩ።

ለነፍሰ ጡር ፣ ለአዳዲስ እናቶች እና ከአምስት ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት በጤና ጥበቃ ሴቶች ፣ ጨቅላዎችና ሕፃናት (WIC) ፕሮግራም በኩል ምግብ ሊያገኙ ይችሉ ይሆናል፡፡ ለ ቋንቋ እርዳታ, በዚህ ስልክ ይደውሉ 1-866-632-9992.

በኮቪድ -19 ወቅት የምግብ ፍላጎት እየጨመረ በመምጣቱ የምግብ ባንኮች ሰዓታቸውን ሊቀይሩ ወይም እግረ መንገዳቸውን ለሚጠቀሙ ሰዎች ዝግ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከመሄድዎ በፊት እባክዎን ይደውሉ። Nortwest Harvest የስቴት ደረጃ የምግብ ባንክ መረብ ነው። የከተማዎን ስም በ ድህረ ገጻችን ለማስገባት በስተ ግራ በሚገኘው አረንጓዴ ሳጥን ላይ ይተይቡ፡፡

በምስራቅ ዋሽንግተን የሚኖሩ ከሆነ የምግብ ባንኮች ዝርዝር በ Second Harvest ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ በአከባቢዎ ያሉ የምግብ ባንኮችን ዝርዝር ለማግኘት ካውንቲዎን በዚህ ድህረ ገጽ ይምረጡ፡፡

መሰረታዊ የምግብ ጥቅማጥቅም ካርዶች

መሰረታዊ የምግብ ጥቅማጥቅም (EBT) ካርዶች ምግብ ለመግዛት ይጠቅማሉ እና ለብዙ ሰዎች ማግኘት የሚቻሉ ናቸው። የU.S. ዜጎች በዋሺንግተን ግዛት Department of Social and Health Services (DSHS) ድረገጽ ላይ መሰረታዊ ምግብ ገጽ የሚለው ላይ ለዚህ ጥቅማጥቅም ማመልከት ይችላሉ።

ማስታወሻ: የፌደራል መንግስት ለተወሰኑ አዋቂዎች የሚሰራውን የስራ መስፈርት በዚህ ችግር ወቅት አግዶታል። ቢሆንም ግን፣ ለዚህ ጥቅማጥቅም ብቁ ለመሆን የፌደራል መንግስት የU.S. ዜጋ መሆንዎን ይጠይቃል።

ከላይ እንደተገለጹት አይነት የዴቢት-ስታይል ካርዶች ሌሎች የፕሮግራም መስፈርቶችን ለሚያሟሉ ብዙ ዜጋ ላልሆኑ ሰዎች ይገኛል። ለዚህ ጥቅማጥቅም በDSHS የመንግስት የምግብ ድጋፍ ፕሮግራም ላይ ማመልከት ይችላሉ (በእንግሊዘኛ ብቻ)።

መረጃ ለቤተሰቦች

ይህ ለመላው ቤተሰብዎ አስጨናቂ ጊዜ ነው፡፡ ይህንን ሁኔታ ከልጆችዎ ጋር እንዴት ማስተካከል እንዳለቦት አንዳንድ ምክሮች እዚህ ያገኛሉ፡፡

የ ቤተሰብ ውይይቶችን በምቹ ቦታዎች ያድርጉ እና የ ቤተሰብ አባሎች ጥያቄ እንዲጠይቁ አበረታታቸው፡፡ የሚረዱትን ቋንቋ ለመጠቀም እና ልዩ ፍርሃታቸውን ወይም የተሳሳቱ አመለካከቶቻቸውን ለመፍታት ከትናንሽ ልጆች ጋር የተለየ ውይይት ለማድረግ ያስቡበት።

ምንም እንኳን መረጃዎን ማወቅ ቢያስፈልግዎትም ፍርሃትን ወይም ሽብርን ሊያሳድጉ ለሚችሉ ሚዲያዎች ወይም ማህበራዊ ሚዲያዎች ተጋላጭነትን ያቀንሱ፡፡ ልጆችዎ በሚዲያ ስለ ወረርሽኙ ተጋላጭነታቸው ምን ያህል ጊዜያቸው በማህበራዊ ድህረ ገጾች ወይም ሚዲያዎሽ እንደሚያሳልፈ ይቆጣጠሩ(ይገድቡ)፡፡

ጥያቄዎችን በማበረታታት እና አሁን ያለውን ሁኔታ እንዲገነዘቡ በማድረግ ልጆችን በመርዳት ላይ ያተኩሩ፡፡

 • ስሜቶቻቸውን እንዲገልጹ ያድርጓቸው እናም ሃሳባቸውን ይቀበሏቸው።
 • በስዕል ወይም በሌሎች እንቅስቃሴዎች ስሜታቸውን እንዲገልጹ ያግዙዋቸው፡፡
 • ቫይረሱ እንዴት እንደሚሰራጭ እና እያንዳንዱ የመተንፈሻ አካላት የሚያጠቃ በሽታ ኮቪድ-19ን ሊያስከትለው የሚችል ኖቬል ኮሮና ቫይረስ አለመሆኑን በተመለከተ የተሳሳተ መረጃ ወይም የተሳሳተ ግንዛቤን ያብራሩ።
 • ምቾት እና ተጨማሪ ትዕግስት ያዳብሩ።
 • በመደበኛነት ወይም ሁኔታው ሲቀየር ከልጆችዎ ጋር እንደገና መገናኘትዎን ያረጋግጡ።
 • የመኝታ ጊዜያት ፣ ምግብ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጊዜ ሲወስድ የቤተሰብዎን ፕሮግራም ወጥነት ይያዙ፡፡፣ እንደ ንባብ ፣ ፊልሞችን ማየት ፣ ሙዚቃ ማዳመጥ ፣ ጨዋታ መጫወትን ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ላይ መሳተፍ ወይም በሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ መሳተፍን (መፀለይ ፣ በአገልግሎት ላይ መሳተፍ) እና እርስዎ እና ቤተሰብዎ በሌሎች አስጨናቂ ሁኔታዎች ውስጥ የተሻሉ እንዲሆኑ ያደረጓቸውን ነገሮች በቤትዎ ለማድረግ ጊዜ ይስሩ፡፡
 • እንደ ብቸኝነት ፣ ድብርት ፣ በሽታ ሊያመጣ ይችላል የሚል ፍርሃት ፣ ጭንቀት ፣ ውጥረት እና ሽብር ያሉ ስሜቶች እንደ ወረርሽኝ ላሉ አሳሳቢ ሁኔታዎች የተለመዱ ምላሾች ናቸው፡፡
 • ከቤተሰብዎ እና ከባህላዊ እሴቶችዎ ጋር በሚጣጣሙ አስደሳች እና ትርጉም ያለው እንቅስቃሴዎች እንዲሳተፉ ቤተሰብዎ ያግዙ፡፡
ተጨማሪ ማጣቀሻ እና መረጃዎች

Washington State Commission on Asian Pacific American Affairs (CAPAA)